"የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገናን የቀን ተቀን አገልግሎት እንዲሆን ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡"

ሀኪሞች ዶት ኮም የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና ከሆነው ከዶ/ር ያየህይራድ መኮንን ጋር ቃለምልልስ አድርጓል፡፡ቃለ ምልልሱን ሎዛ አድማሱ እንደሚከተለው አዘጋጅታ አቅርባልናለች፣ ተከታተሉት፡፡   ሀኪሞች:- ራስህን አስተዋውቀን፡፡ ስሜ ዶክተር ያየህይራድ መኮንን ይባላል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪዬን በ ሜዲስን (ሰባት አመት) እና ስፔሻሊቲ በ ጠቅላላ ቀዶ ህክምና (አራት አመት)፣ በአጠቃላይ 11 አመት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ነበርሁ፡፡ ከ 2012-2017 G.C. ጠቅላላ የልብ ቀዶ ህክምና ( General Cardiac Surgery)ን እስራኤል ሀገር አጥን...
Continue reading
  1313 Hits
  0 Comments
1313 Hits
0 Comments

ከልብ ሕመም ለመታደግ

ማዕከሉ ከተመሠረተ ጀምሮ ከ5,800 በላይ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት እንዳገኙና በአሁን ወቅትም ከ4,600 በላይ ታማሚዎች ወረፋ ይዘዋል፡፡ የልጅነት ዕድሜያቸውን በቅጡ ቦርቀው ሳይጨርሱ በልብ ሕመም የሚሰቃዩትን ለመታደግ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች የመጡ ሕፃናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፣ እየሆኑም ነው፡፡ ነገር ግን ማዕከሉ በተለይ የግብዓትና የገንዘብ ችግር አለበት፡፡ በማዕከሉ ...
Continue reading
  521 Hits
  0 Comments
521 Hits
0 Comments

ከሰባት ሺሕ በላይ የልብ ሕሙማን ሕፃናት ለቀዶ ሕክምና ወረፋ እየተጠባበቁ ነው›› አቶ ሳላዲን ከሊፋ፣ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማኅበር ፕሬዚዳንት

 አቶ ሳላዲን ከሊፋ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማኅበር ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ በማኅበሩ አመሠራረትና በልብ ሕሙማን ሕፃናት ሕክምና ማዕከል እንቅስቃሴ ዙሪያ  ማብራሪያ ቢሰጡን?  የልብ ሕሙማን ሕፃናት ሕክምና ማዕከል ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ አመሠራረቱን በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጡን? አቶ ሳላዲን፡- ከማዕከሉ አመሠራረት በፊት ስለ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማኅበር እንቅስቃሴ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ማኅበሩ ከተመሠረተ 30 ዓመት ሆኖታል፡፡ ከዚህም ውስጥ ለ20 ዓመት ያ...
Continue reading
  500 Hits
  0 Comments
500 Hits
0 Comments

የእስራኤል የልብ ህክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ህክምና ሊሰጡ ነው

 ኅዳር 9 /2012 መቀመጫውን እስራኤል ያደረገው 'ሴቭ ኤ ቻይልድ'ስ ኸርት የተባለና ለትርፍ ያልተቋቋመው አለም አቀፍ የልብ ህክምና ቡድን ነገ በኢትዮጵያ የልብ ህከምና ማዕከል አገልግሎቱን ይሰጣል። ቡድኑ ለ30 ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና እና ሌሎች ተያያዥ ህክምናዎችን እንደሚሰጥ ፒአር ኒውስ ከዋሽንግተን ዘግቧል። 'የህፃናትን ልብ ማዳን' የሚል ተልዕኮ ያነገበው ቡድን በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ከሚሰሩትና የቡድኑ አጋር ከሆኑት ዶክተር ያየህይራድ መኮንን ጋር በመሆን በማዕከሉ ህክምናውን ይሰጣል ተብሏል። የቡድኑ አባላት በቆይታቸው ለህፃናት ...
Continue reading
  659 Hits
  0 Comments
659 Hits
0 Comments

‹‹ለልብ ልብ ይበሉ››

የልብ በሯ ከውጭ የምትገባው በትንሹ አንድ ሺሕ ዶላር ተከፍሎባት ነው፡፡ ሳምባና ልብን ተክቶ የሚሠራው መሣሪያ ላይ የሚገጠሙ ደም ማመላለሻቱቦዎችና ማጠራቀሚያ ከአንድ ጊዜ በላይ ጥቅም ላይ መዋል አይችሉም፡፡በታካሚው ቁጥር ልክ ሊኖሩ ግድ ይላል፡፡ ይሁንና የታካሚውንና የግብዓት አቅርቦቱን ቁጥር ማመጣጠን እስካሁን አልተቻለም፡፡ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ ለአንድጊዜ የሚገለገሉበትን የሚገዙት ከአንድ ሺሕ እስከ 2,000 ዶላር አውጥተው ነው፡፡ ለህክምው ወሳኝ የሚባሉ ሌሎችም የአላቂ ዕቃዎችና መድኃኒቶች አቅርቦትውስንነት በመኖሩ በአግባቡ አገልግሎት እንዳይሰጥ...
Continue reading
  413 Hits
  0 Comments
413 Hits
0 Comments