News

 በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ኢትዮጵያ በመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ 50 በመቶ ራሷን ትችላለች ቢባልም አሁን ያለችው 20 በመቶ ላይ መሆኑን የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ አስታወቀ ።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሎኮ አብርሃ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተጠየቅ ዓምድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት በመድኃኒት ዘርፉ ላይ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን አገሪቱ በእቅድ ዘመኑ 50 በመቶ ራሷን ትችላለች ቢባልም ማሳካት አልተቻለም።ዶክተር ሎኮ ‹‹ዛሬም የሚያሳስበንና የምናስመ ጣቸው መድኃኒቶች በጣም የቆዩትን እንደ አሞክሳ ሲሊ...
 የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ አለመሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የማህበረሰብ ንቅናቄን በመፍጠር ግንዛቤው ከፍ እንዲል እንደሚሰራም ጠቁሟል።በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእናቶችና የህጻናት ጤና ዳይሬክቶሬት የቤተሰብ እቅድ ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ ግርማ ገመቹ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፡የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ቢሆኑምበተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ፖለቲከኞች ጉዳዩን አጀንዳ በማድረግ ህብተረተሰቡን ማደናገራቸው ስራው በሚፈለገው ልክ ውጤታማ...
 በአፍሪካ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽንና ኮንፍረንስ ከህዳር 22 እስከ 24/2012 ዓ.ም ‹‹ለጤናዬ እጠነቀቃለሁኝ›› በሚል መሪ ቃል በሚሌኒየም አደራሽ ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ የግል ጤና ተቋማት አሰሪዎች ማህበር አስታወቀ፡፡ማህበሩ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኤግዚቢሽኑ በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵ የመጀመሪያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ ጌቱ ቢሳው እንደገለፁት በታላቁ የጤና ኤግዚቢሽንና ኮንፍረንስ ላይ ነፃ የህክምና ምርመራ እንደሚካሄድ ጠቁመው በቀን ለ...
 የዓድዋ ሪፈራል ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ በላይ በመጓተቱ ምክንያት የተሟላ የጤና አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ።ግንባታውን የሚያከናውነው የዛምራ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በበኩሉ በተሰጠው 600 የሥራ ቀናት ስራውን ጨርሶ ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል።የአድዋ ከተማ ምክር ቤት አባል አቶ ተሻለ መስፍን እንዳሉት የከተማው ህዝብ ለረዠም ዓመታት የመሰረተ ልማት ፍላጎት ጥያቄውን ሲያነሳ ቆይቷል።በእዚህም የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለ...
 አዲስ አበባ ኢዜአ ህዳር 16 /2012 በኢትዮጵያ የስኳር ህመም የሚያስከትለውን ማህበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ ችግር ለማቃለል የህሙማን ቤተሰብን ማእከል ያደረገ የመከላከል ተግባር ማከናወን ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር አሳሰበ።29ኛው የዓለም የስኳር ህመም ቀን "የስኳር ህመም ቤተሰቤን ይመለከታል" በሚል መሪ ሐሳብ በመከበር ላይ ነው።ከቀኑ ጋር በተያያዘ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ውይይት ላይ እንደተገለፀው 70 በመቶ የሚሆነው የስኳር ህመም መከሰቻ መንገድ ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዘ በመሆኑ በተለይ በአንድ ጎጆ ስር የሚ...
 ሕዳር 17፣ 2012/ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነፃ ህክምና ልሰጥ ነው አለ::ከሕዳር 15 ጀምሮ የታካሚዎች ምዘገባ እየተካሄደ ነው፡፡Listen to the audio below.source
 ህፃን ልጃቸውን በአቢሲኒያ ጤና ጣቢያ ሲያስከትቡ ያገኘናቸው ወይዘሮ ነጻነት ተረፈ የመርካቶ ሰባተኛ አካባቢ ነዋሪ ናቸው። ወይዘሮ ነፃነት ሁለት ጊዜም የእርግዝና ክትትል ያደረጉት በመሳለሚያ ጤና ጣቢያ እንደነበር ያስታውሳሉ። የሦስት ወር እርጉዝ ከሆኑ አንስቶ የእግርዝና ክትትል ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ዘጠነኛ ወራቸው እንደ ደረሰ የፅንሱም የእሳቸውም ክብደት ይጨምራል። በዚህ የተነሳም የደም ግፊታቸው ከፍ ማለቱ ይነገራቸዋል።በሆስፒታል ደረጃ መታየት እንዳለባቸውም ይገለጽላቸውና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ይላካሉ። ሆስፒታል ደርሰውም ምጡ ይጠናባቸው...
 ኢዜአ ህዳር 15 /2012ዓ.ም የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ኤች አይ ቪ ኤድስን ቀድሞ መከላከል ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።የምክር ቤቱ የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የጽህፈት ቤቱን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ገምግሟል።በዚሁ ወቅት እንደተገለጸው፤ የበሽታው የስርጭት አማካይ መጠን በአገር አቀፍ ደረጃ 0 ነጥብ 9 ሲሆን ስርጭቱ የከተማው ከገጠር በ7 እጥፍ ይበልጣል።በከተማ ስርጭቱ 3 በመቶ ሲሆን በማረሚያ ቤቶች፣ በሴተኛ አዳሪዎችና የረጅም ርቀት መኪና አሽከ...
 ኢዜአ ህዳር 16/12 ዓ/ም በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንዲገኝ እንዳደረገው የክልሉ ጤና ቢሮና አጋር ተቋማት ገለጹ።በትግራይ ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ የስራ ሂደት ባለቤት አስተባባሪ አቶ ፍስሃ ብርሃነ እንዳሉት በሽታውን ለመከላከል በክልሉ ውስጥ ቀደም ሲል የነበሩ እንቅስቃሴዎች እየተቀዛቀዙ መጥተዋል።በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቀደም ሲል በየደረጃው ባሉ መንግስታዊና አጋር ተቋማት የነበረውን ቅንጅታዊ አሰራር ...
 ኢዜአ/ ህዳር 16 /2012 የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከህንድ አገር ከሚመጡ ስፔሻሊስት ዶክተሮች ጋር በመተባበር ህክምናን በነጻ ሊሰጥ ነው።የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ አምብሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ሆስፒታል ከህንድ አገር ከሚመጡ ስፔሻሊስት ዶክተሮችጋር በመተባበር የዓይን፣ የጥርስ፣ የሆድ ዕቃ፣ የፊንጢጣ፣ የወንድ የዘር ፍሬ ከረጢትና የአንጀት መውረድ ቀዶ ህክምና ለመስጠት አቅዷል።ህክምናው የሚሰጠው ከህዳር 19 እስከ 21 ቀን ድረስ የሚቆይ የነጻ የህክምና አገልግሎት ሲሆን ለዚህም ዝ...
St. Paul's Hospital Millennium Medical College-SPHMMC - have a good NEWS."We are pleased to announce that Dr.Bethel Dereje of SPHMMC certified by German Society of for Gynecological Oncology (AGO) as Gynecologic Oncologist. Congratulations!"SOURCE
 As a member, you understand the value of belonging to EMA. Now, more than ever, EMA is playing a critical role in advocating on behalf of the physicians, and providing enhanced professional development opportunities.Recruit 10 or more new members between November 20, to December 22, 2019 and you will be automatically entitled for the training...
 የሕክምና ባለሞያዎች ከሀገር ወጥተው እንዲሰሩ የሚያስችለው መመሪያ አሁንም በረቂቅ ደረጃ ያለ ቢሆንም መመሪያው ፀድቆ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ግን በደንብ ሊታይ ይገባል ተባለ፡፡ባለሞያዎች የሚያገለግሉባቸው ሐገራት ገና አልተለዩም፤ ስምምነትም አልተደረሰም ብሏል የጤና ሚኒስቴርበሐገር ቤት ያለው የጤና ባለሞያ ቁጥር ተስተካክሎ እንጂ እጥረት በሚታይባቸው እና ሐገሪቱም ተጨማሪ በምትፈልግባቸው የህክምና ዘርፎች ባለሞያዎች ከሐገር ወጥተው እንደማይሰሩም ተነግሯልDr. Gemechis, EMA current president, shared his opinion ...
 ሰመራ (ኢዜአ) ህዳር 12 ቀን 2012ዓ.ም በአፋር ክልል የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከመጣ የዓይን ሕክምና ቡድን ጋር በመተባበር ለሕብረተሰቡ የነጻ ዓይን ሕክምና በመስጠት ላይ መሆኑን አስታወቀ።የነጻ ሕክምና አገልግሎቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 500 ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።የሕክምና ቡድኑ አስተባባሪ አቶ በላይ በለጠ እንዳሉት በነጻ አገልግሎቱ ከዕድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ለሚከሰተው የዓይን ሞራ ግርዶሽና ሌሎች የዓይን ሕመሞች ሕክምና ይሰጣል።ሕክምናው ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ ያለው የዓይን ስፔሻ...
 ሕዳር 12፣ 2012/ በጆሮ ህክምና ላይ የሚመክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው ተባለየጆሮ ሕመም ችግር የሰፋ ቢሆንም በዘርፉ የሰለጠነ ስፔሺያሊስት ሐኪሞች ቁጥር ግን ተመጣጣኝ አይደለም ተብሏል፡፡The 3rd ENT conference. Listen to the audio news from Sheger FM.source
 በ2019 በዴሞክራቲክ ኮንጎ ያጋጠመውና በመላ አገሪቱ የተዛመተው የኩፍኝ ወረርሽኝ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ።የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው በዴሞክራቲክ ኮንጎ ያጋጠመው የኩፍኝ ወረርሽኝ በዓለማችን ፈጣኑ ወረርሽኝ ነው። ወረርሽኙ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ኢቦላ ባለፉት 15 ወራት ከገደላቸው ሰዎች ሁለት እጥፍ የሚሆኑ ዜጎችን ሕይወት ቀጥፏል።የአገሪቱ መንግሥት የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት መስከረም ላይ በጀመሩት የድንገተኛ የክትባት ፕሮግራም እስከ 8 መቶ ሺህ የሚደርሱ ህጻናትን ለመከተብ ታስቦ ነበር።ነገር ...
 አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት መጀመሪያው ሩብ ዓመት በጤናው መስክ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የጤና ሚኔስቴር አስታወቀ።በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክትር ተገኔ ረጋሳ እንደገለጹት፥ በበጀት ዓመቱ የእናቶች ጤናን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።በዚህ መሰረትም የቤተሰብ እቅድ አፋጻጸም 67 በመቶ መድረሱን እና የቅድመ ወሊድ ክትትል ላይ ደግሞ 65 በመቶ መሰራቱን አብራርተዋል ፡፡ከድሬዳዋ አስተዳደር በስተቀር በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በ32 ወረዳዎ...
 ኢዜአ ህዳር 12 / 2019 ዓ.ም በመንግስት የጤና ተቋማት የሚስተዋለውን የመድሃኒት እጥረት ለመቀነስ ኅብረተሰቡ ህገ ወጥ የመድሃኒት ዝውውርን በጋራ እንዲከላከል የጤና ሚኒስቴር ጠየቀ።የጤና ሚኒስቴር በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫውም በአገሪቷ ወደ መንግስት ጤና ተቋማት በመሄድ ህክምናቸውን የሚከታተሉ ዜጎች "መድሃኒቱ የለም ወይም አልቋል" በሚል ሰበብ ከግል መድሃኒት ቤቶች እንዲገዙ ይገደዳሉ።በዝቅተኛ ኢኮኖሚ የሚተዳደረውና መድሃኒት በውድ ዋጋ እንዲገዛ የተገደደ...
 አዲስ አበባ ኅዳር 11 ቀን 2012 በኢትዮጵያ ለህጻናት መቀንጨር ችግር ተቋማት እኩል ትኩረት አለመስጠታቸው የሚፈለገው ውጤት እንዳይመጣ ማድረጉን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።ሚኒስቴሩ የ2011 ዓመት ብሔራዊ የስርአተ- ምግብ መርሃ ግብር አፈጻጸምን ከክልል ጤና ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በአዲስ አበባ እየገመገመ ነው።በ2011 እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት መቀንጨርን ከነበረበት 38 በመቶ ወደ 31 በመቶ ዝቅ ለማድረግ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ማሻሻል የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።በመሆኑም የ2019 የስነ ህዝብ...
 የተመድ እስከ ጎርጎሪዮሳዊው 2030 ድረስ ለማሳካት በልማት ግብነት ከያዛቸው አጀንዳዎች አንዱ የሴቶችን የስነተዋልዶ ጤና የማዳረስ፤ ከላየ ፅንስ የሚጠቀሙ እናቶችን ቁጥር የማበራከት እግረ መንገዱንም በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ለሚሄደው የሕዝብ ቁጥር መፍትሄ ማበጀት ይጠቀሳል።ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በተለይ በወሊድ ጊዜ ሕይወታቸውን የሚያጡ እናቶችን ቁጥር ለመቀነስ የታለመው ያስገኘው ውጤት እና ተያያዥ ጉዳዮች በቅርቡ ኬንያ ላይ ተገምግመዋል። ባለፈው ሳምንት ከኅዳር 2 እስከ 4 ለሦስት ቀናት ናይሮቢ ኬንያ ላይ የተካሄደው ጉባኤ በዚህ ...